Announcement

ቀን፡- 07/05/2013ዓ.ም

 

ማስታወቂያ

ለግብይት ፈጻሚዎች በሙሉ

 በውክልና የተሰጡ ስራዎችን ስለማሳወቅ

ብሔራዊ ግብይት ፈፃሚዎች ማኅበር የግብይት ተዋንያን አቅም በመገንባትና የሚጠበቅበትን የክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ ስራ በማጠናከር የእርስ በእርስ ቁጥጥር ኃላፊነቱን በተሻለ ደረጃ መወጣት ይችል ዘንድ እስካሁን በባለስልጣኑ ሲከናወኑ ከነበሩ ስራዎች ውስጥ በውክልና ለማህበሩ መስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በመሆኑም ከየካቲት 1/2013ዓ.ም ጀምሮ በባለስልጣኑ ይሰጥ የነበረው፡-

  1. የግብይ ወኪሎች አዲስም ሆነ ነበር የእውቅና እድሳት አገልግሎት ስራ

ከአመታዊ የኦዲት ሪፖርት በስተቀር የሩብ አመት የፋይናንስ አቋም፣ የግብይት ተሳትፎ እና የደንበኞች ዝርዝር መረጃ ሪፖርቶችን የመቀበልና የማደራጀት ስራ ለብሔራዊ ግብይት ፈፃሚዎች ማህበር በውክልና የተላለፈ መሆኑን አውቃችሁ በማህበሩ ጽህፈት ቤት በመቅረብ እንድትስተናገዱ እናሳውቃለን፡፡