የኢትዮጵያን ዘመናዊ የምርት ግብይት አሰራርን መልካም ተሞክሮ ለመቀመር የማላዊ እና የሞዛምቢክ የምርት ገበያና የባንክ የስራ ሃላፊዎች የባለሥልጣኑ የቁጥጥር አና ክትትል ስራ በተመለከተ ማብራሪያ ቀርቦላቸዋል፡፡

የማላዊ ማዕከላዊ ሪዘርብ ባንክ የልኡካን ቡድን አባል የሆኑት አቶ ዲክሰን ማሳዋ እንደገለጹት የኢትዮጵን ዘመናዊ የግብርና ምርት ግብይት በአፍሪካ ደረጃ መልካም ዝናን ያተረፈ በመሆኑ  ዘመናዊ የምርት ግብይትን የሚያስፈጽሙ ተቋማት በአገራቸውን ለማቋቋም የተሻለ ተሞክሮ ለመቅሰም እንደመጡ ተናገረዋል፡፡.

በዚህም መሰረት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን ኢንጂነር ዑሌሮ ኡፒየው አጠቃላይ የግብይት ስርዓቱን አሰራር እና አሁን የደረስንበት ደረጃ ለቡድቡ አስረድተዋል፡፡ የሞዛምቢክ ምርት ገበያ ሊቀመንበር የሆኑት  ወ/ሮ ቪክቶሪያ ፓውሎ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በአለም አቀፍ ደረጃ መልካም ስም ያለው እና ዕውቅናን ያተረፈ ነው፡፡ በአገራቸው በመንግስት የተቋቋመው  የሞዛምቢክ ምርት ግብይት አምስት ዓመታት ያስቆረጠ አዲስ ገበያ በመሆኑ ጠቅሰው ጉብኝቱ አነስተኛ አምራች አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ልምድ ለመቅሰም መቻላቸው ተናግረዋል፡፡

የልዑካኑ ቡድኑ በተመሳሳይ በምርት ገበያው ተገኝተው አሰራሩንና የቅምሻ ማዕከሉን በመጎብኘት ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡