ወደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ድረ-ገፅ እንኳን ደህና መጡ!

Amharic amh English Eng

የሚዲያ ባለሙያዎች

የሚዲያ ባለሙያዎች ዘመናዊ የምርት ግብይት አሰራር ላይ በተግባር የተደረፈ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በአማራና በትግራይ ክልሎች የሰሊጥ የመጀመሪያ ደረጃ የግብይት ማዕከላት፣የኢትዮጵያ ግብርና ምርቶች የመጋዘን አገልጎልት ድርጅት እና የምርት ገበያው የኤሌክትሮኒክ ግብይት አሰራርን ከየካቲት 21 እስከ መጋቢት 02 ቀን 2008ዓ.ም የተካሄደ ትምህርታዊ ጉብኝት


የባለስልጣኑ የ2008 ዓ.ም የውጤት ተኮር እቅድ ሰነድ ርክክብ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት(2008-2012 ዓ.ም) የሚመራበትን ስትራቴጂያዊ እቅድ ሰነድ መሰረት በማድረግ በየሥራ ክፍሎች የተዘጋጁትን የ2008 ዓ.ም የውጤት ተኮር እቅድ ሰነዶች የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ተረከቡ፡፡Read More


በትግራይ ክልል በ2006-2007 የምርት ዘመን የሰሊጥ ቁጥጥር አፈፃጸም ደካማ እንደነበረ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ከትግራይ ክልል አስተዳደር ጋር በመተባበር መስከረም 22 እና 23 ቀን 2008 ዓ.ም በሽረ እንዳስላሰ ከተማ ባካሄደው የክልሉ የባለድርሻ አካላት የምክክርና የግምገማ መድረክ ላይ እንደተገለጸው የኮማንድ ፖስት(የግብረኃይል አባላትና) እና ባለሙያዎች የሰሊጥና የነጭ ቦለቄ ደንብን በመተግበር ረገድ ያደረጉት እንቅስቃሴ ደካማ ነው፡፡Read More


ለብሔራዊ የግብይት ፈጻሚዎች ማኅበር መጠናከር ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ

በጥቅምት ወር መጀመሪያ በተካሄደው ሁለተኛው ብሔራዊ የግብይት ፈጻሚዎች ማኅበር ኤግዚብሽንና ኮንፈረንስ ላይ የተገኙት የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ያእቆብ ያላ እንደተናገሩት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ስለ ብሔራዊ የግብይት ፈጻሚዎች ማኅበር ያላቸው ግንዛቤና ድጋፍ አነስተኛ በመሆኑ ማኅበሩ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት በተሟላ ሁኔታ ተወጥቷል ማለት አይቻልም፡፡Read More


የግብይት ተሳታፊዎችን የተመለከቱ የአሰራር ማሻሻያዎች መደረጋቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣንና በምርት ገበያው በሚካሄዱ የእውቅናና ቅድመ እውቅና አሰጣጦች እንዲሁም ከአባልነት መብት ጋር በተያያዘ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት የአሰራር ማሻሻያዎች መደረጋቸው ተገለፀ፡፡Read More


የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓት በይፋ ተጀመረ

የግብይት ሥርዓቱን በማዘመን ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው የሚጠበቀው የኤሌክትሮኒክ የግብይት ሥርዓት ከሙከራ ትግበራ በመውጣት በይፋ መጀመሩን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታወቀ፡፡Read More


የኢትዮጵያ የግብርና ምርቶች የመጋዘን አገልግሎት ድርጅት ሥራውን በይፋ ጀመረ

በሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር 331/2007 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ የግብርና ምርቶች የመጋዘን አገልግሎት ድርጅት የአደረጃጀት እና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ከጥቅምት 1/2008 ዓ.ም ጀምሮ ሥራውን በይፋ መጀመሩ ተገለጸ፡፡Read More


አጫጭር ዜናዎች

15 Nov 2015 በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ(GTP I) አፈጻጸምና በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ(GTP II) ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡Read More


 

በጌዴኦ ዞን የቡና ምርታማነትን በሄክታር 18 ኩንታል ለማድረስ ታቅዷል

15 Nov 2015 ኢኮኖሚ ዲላ ህዳር 5/2008 በጌዴኦ ዞን በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መጨረሻ የቡና ምርታማነትን በሄክታር 18 ኩንታል ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ በእቅድ ዘመኑ አርሶ አደሩን በጥምር ግብርና በማሳተፍ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን ይሰራል። በዞኑ የ2008 ዓ.ም ዕቅድ የፈፃሚ ማዘጋጃ ንቅናቄ መድረክ ማጠቃለያ ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ደምሴ እንደጠቆሙት ከአምስት አመት በፊት የዞኑ የቡና ምርታማነት በሄክታር ከአራት ኩንታል ያልበለጠ ነበር።Read More

በአማራ ክልል የመጀመሪያ የሆነ የቡና ልማትና ግብይት ህብረት ስራ ማህበር ዩኒየን ተቋቋመ

10 Nov 2015 ኢኮኖሚ ባህር ዳር ጥቅምት 30/2008 በአማራ ክልል ቡናን በብዛትና በጥራት አምርቶ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ገለጹ። በክልሉ የመጀመሪያ የሆነው የቡና ልማትና ግብይት ህብረት ስራ ማህበር ዩኒየን ትላንት በባህርዳር ተቋቁሟል። Read More

ECX takes Ethiopia's Agri-market to a New Leap

This month the Ethiopia Commodity Exchange embarked on a new course with its inauguration of eTRADE platform, the first of its kind in the country. The platform is expected to break the physical and time barrier of the current trading arrangement and economies-of-scale for further expansion to trade in additional new commodities. Read More

የGTP-1 አፈፃፀምና GTP-2 እቅድ ውይይት

ንግድ ምንስቴር የአራት ቀን ከ27/01/2008 – 02/02/2008 ዓ.ም የGTP-1 አፈፃፀምና GTP-2 እቅድ ላይ ውይይት አደረገ፡፡ ክቡር ምኒስትር አቶ ያቆብ ያላ የውይይቱ መድረክ በመከፈት ሁለተኛው የትራንስፎርሜሽን እቅድ አበይትና ቁልፍ ስራዎችን በመተንተን ሠራተኛው ሰፊ ግንዛቤ እንድያገኝ አድርገዋል፡፡

Eng
Eng
Eng


ራዕያችን

በ2020 በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ፣ ዜጎችን የሚያሳትፍና ተጠቃሚ የሚያደርግ የምርት ግብይት ሥርዓት ተገንብቶ ማየት፡፡

ተልእኳችን

የዘመናዊ ምርት ገበያ መርሆዎች በህብረተሰቡ እንዲሰርጽ በማድረግ፣ የገበያ ሥርዓቱን የሚያናጉ እንቅስቃሴዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር በአገሪቱ ፍትሃዊ፣ ግልጽና የተቀላጠፈ የምርት ገበያ ሥርዓትን መዘርጋትና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ማረጋገጥ ነው፡፡

 


image

የአገሪቱን እድገትና ልማት ቀጣይነት ለማረጋገጥ መንግሥት ግብርና መር ኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ቀይሶ ከዚህም የሚመነጩ የተለያዩ የልማት ፖሊሲዎችና የዘርፍ ስትራቴጂዎች ነድፎ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህም ስትራቴጂ በገበያ የሚመራ የግብርና ልማት እንዲኖር የምርት ግብይት ሥርዓቱን ዘመናዊና ፍትሃዊ በማድረግ ልማቱን ማቀላጠፍ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን ውጤታማ የሆነ የግብይት ስርዓት መገንባቱን የማረጋገጥ፣ የምርት ገበያው አስተማማኝ፣ ግልፅና የተረጋጋ አሰራር እንዲኖረው የማረጋገጥ እንዲሁም የሻጮችን፣ የገዥዎችን፣ የአገናኞችንና በአጠቃላይ የህብረተሰቡን መብትና ጥቅም የማስጠበቅ ዓላማዎችን ለማስፈፀም በአዋጅ ቁጥር 551/1999 ተቋቁሟል፡፡ ተጨማሪ


ስለ ኢትዮጲያ ምርት ገበያ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ ቢሆንም እንደአስፈላጊነቱ በሌሎች ቦታዎች ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ሊኖሩት እንደሚችል በባለስልጣኑ ማቋቋሚያ አዋጅ 551/1999 ተገልጿል፡፡ ስለሁነም ፣የምርት ገበያው አስተማማኝ፣ግልጽና የተረጋጋ አሰራር እንዲኖረው ባላሰልጣኑ በቅርቡ በክልሎች ሶስት ማስተባበሪያ ፅ/ቤቶችን ከፍቷል

ኢምገባ የተቋቋመው ዘመናዊ የምርት ግብይት ሥርዓት በአገሪቱ መገንባቱን ለማረጋገጥ፣ የምርት ገበያው አስተማማኝ፣ ግልፅና የተረጋጋ አሰራር እንዲኖረው ለመቆጣጠር፣ እንዲሁም የሻጮች፣ የገዥዎችን፣ የአገናኞችንና በአጠቃላይ የህብረተሰቡን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሆን ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነቱም፡

1.ለክፍያ መፈጸመሚ ተቋማት እውቅናን የመስጠት ወይም የመንሳት

2.ለግብይት መፈጸመሚዎች እውቅናን የመስጠት ወይም የመንሳት

3.የምርት ገበያን የክፍያ መፈፀሚያ ተቋማትንና የግብይት መፈጸመሚዎችን ቁጥጥር በተመለከተ መመሪያዎችን የማውጣት እንዲሁም ይህንኑ በተመለከተ ምርምራ የማጽደቅና ትክክለኛነቱነ የማለጋገጥ ስልጣኑን ተግባራዊ የማድረግ

4.ከምርት ገበያ ስራ ጋር በተያያዘ የኢነቨስትመንት አማካሪያችን የአማካሪ ድርጅቶችን የህግ ባለሙያዎችን የሂሳብ አዋቂ ባለሙያዎችን አሰራር የመቆጣጠር

5.የምርት የግብይት ውሎችን ዝርዝር ይዘት ሽያጭና ግዢ መርሆችን በሚመለከት መመሪያ የማውጣት

6. የምርት የግብይት ውሎችን ክፍያና ርክክብ አፈጻጸምን የመቆጣጠር

ተጨማሪ